Post Job Free
Sign in

Mco

Location:
Ethiopia
Salary:
23000
Posted:
December 11, 2023

Contact this candidate

Resume:

ቀን **/**/**** ዓ.ም

ቁጥር MCO/***/****

ለተልዕኮ ለትውልድ ቤ/ክ

ምዕራብ አባያ(ብርብር)

ጉዳዩ:- የአጥቢያዋ አሁናዊ ሁኔታን በመገምገም የተሰጠ የውሳኔ ሀሳብን ስለማሳወቅ

ተልዕኮ ለትውልድ ቤ/ክ ዋና ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የቤተክርስቲያኒቱን እንቅስቃሴ በተቀመጡ ምሪትና አቅጣጫዎች መሰረት እየተከናወኑ ስለመሆናቸው በመከታተል ለውሳኔ ግብአት የሚሆኑ መረጃዎችን እና ጥናቶችን በማድረግ አስፈላጊ የእርምት ተግባራትን እንደሚወስድ ይታወቃል

በዚሁ መሰረት የምዕራብ አባያ አጥቢያ ያለችበትን ሁኔታ አጣርቶ ውሳኔዎች መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የኔትወርኮች ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት መጋቢ ተስፋጽዮን ዳዊት ሐሙስ ህዳር 06 ቀን 2016 ዓ.ም በምዕራብ አባያ (ብርብር) ከተማ ባደረጉት የመስክ ጉብኝት ሪፓርት መሠረት በአጥቢያው ላይ እና በተጀመረው የትምህርት ቤት ግንባታ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት ለማስተካከል እንዲቻል የሚከተሉት ውሳኔዎችን ተግባራዊ እንዲደረግ አዝዣለሁ

1. የትምህርት ቤቱን ግንባታ በተመለከተ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር የተካተቱበት ባለ 5 የግንባታ ኮሚቴ አባላት ተዋቅሮ ወደ ስራ እንዲገባ

2. በአጥቢያው ላይ የተፈጠረውን የህዝብና የፋይናንስ መቀነስ ችግር ለመቅረፍ በየሳምንቱ ሰኞ ዕለት የአርባምንጭ አጥቢያ ዋና መጋቢ ሰለሞን ቡራቃ አጥቢያው ላይ የፈውስና የትንቢት አገልግሎት እንዲጀምሩ

4. በመጨረሻም የአርባምንጭ አጥቢያ በልዩ ትኩረት ምዕራብ አባያን እንዲከታተል እና ለወላይታ ሶዶ ኔትወርክ አስፈላጊውን ሪፖርት እንዲያቀርብ አዝዣለሁ

ከሰላምታ ጋር

ግልባጭ

ለኔትዎርኮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

ለተልዕኮ ለትውልድ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት

ለወላይታ ሶዶ ኔትወርክ

ለአርባ ምንጭ አጥቢያ

ቀን 15/03/2016 ዓ.ም

ቁጥር MCO/038/2016

ለመጋቢ አንዳርጋቸው እሸቱ

ምዕራብ አባያ/ብርብር

ጉዳዩ - የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠትን ይመለከታል

ተልዕኮ ለትውልድ ቤ/ክ ዋና ጽ/ቤት የመጋቢዎችና የልዩ ልዩ ክፍል አገልጋዮችን ስነምግባር ደንብ አዘጋጅቶ አገልጋዮችን ሰራተኞች እንዲያውቁትና እንዲተገብሩት በማድረግ እንዲሁም ይህንን የተላለሩ ግለሰቦችን የእርምት እርምጃ እንደሚተገብር ይታወቃል

በዚሁ መሰረት የኔትወርኮች ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት መጋቢ ተስፋጽዮን ዳዊት በመስክ ጉብኝት ሐሙስ ህዳር 06 ቀን 2016 ዓ.ም በምዕራብ አባያ(ብርብር) ከተማ ባደረጉት የመስክ ጉብኝት መሠረት እርስዎ በተደጋጋሚ ከተማውን ጥለው በመውጣት እንደመጋቢ ማድረግ ሲገባዎት ከቤተክርስቲያን የጠፉ ሰዎችን ባለመፈለግ እና የተሰጠዎትን ኃላፊነት በአግባቡ ባለመወጣትዎ ምክንያት የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ የፋይናንስ አለመኖር እና የተጀመረው የትምህርት ቤት ግንባታ ምንም አይነት ለውጥ ሳይታይበት ወራትን ማሳለፉ ታውቋል ይህም ለቢሮአችን ሪፓርት ቀርቧል

በዚህ ምክንያት ይህ የመጨረሻ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠዎት መሆኑን እያስታወቅሁ የተጠቀሱትን ክፍተቶች በፍጥነት የማያስተካክሉ ከሆነ ከኃላፊነትዎ የሚነሱ መሆኑን በጥብቅ አሳስባለሁ

ከሰላምታ ጋር

ግልባጭ

ለኔትዎርኮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

ለተልዕኮ ለትውልድ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት

ለወላይታ ኔትወርክ

ለምዕራብ አባያ አጥቢያ



Contact this candidate