Post Job Free
Sign in

1 2 3

Location:
Addis Ababa, Ethiopia
Posted:
April 25, 2024

Contact this candidate

Resume:

አንቀጽ *

መግቢያ

ኢትዮጵያውያን ከምንኮራባቸው ቅርሶቻችን መሀል የተለዩና የዳበሩ ባህላዊ ትውፊቶች ባለቤትነታችን ይገኝበታል ከነዚህ ባህላዊ ሀብቶች መሀል ደግሞ በተለይም ዕቁብና ዕድር ልዩ መገለጫዎቻችን ናቸው ዕድር መሰረቱ የሰፋ ፋይዳውም የላቀ እሴታችን ነው ስለዕድር ስናነሳ ስለግሩም ታሪክና ባህላችን ማውሳታችን ነው ስለአብሮነት ስለመተሳሰብና ስለፍቅርም ማውራታችን ይሆናል ማህበራዊና ስነልቦናዊ መቻቻላችንንም የሚያስታውስ ልዩ የማንነት መገለጫችንም ጭምር ነው

የመልካም ልሳን ወጣቶች መረዳጃ ዕድር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚኩራ ወረዳ 02 ልዩ ስሙ ሀያት 2 የጋራ መኖሪያ መንደርና በአካባቢው በሚኖሩ ወጣቶችና ጎልማሶች ለማህበራዊ ትስስር የተፈጠረ የመረዳጃ ዕድር ሲሆን ከተቋቋመበት የመመስረቻ ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ/ም አንስቶ የተለያዩ ጅማሮ የሆኑ ተግባራትን በማከናወን በአካባቢውም ብሎም በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት በማግኘት የእርስ በእርስ የመረዳዳት ባህልን እየጠነከረ የሚሄድ የመረዳጃ ዕድር ነው

ጥንታዊ አባት እናቶቻችን ዕድርን ሀሳብ ሲፀነሱ ዓይነታውን ትኩረት ለማህበራዊ ፋይዳው የሰጡ ይመስላሉ ህይወትና ሞት ህብር ፈጥረው የሚዘልቁ የተፈጥሮ ሂደቶች ናቸውና ከህልፈት በፊት ህይወትን የማድመቁን አስፈላጊነት ከማህበር አወቃቀራቸው መረዳት አይከብድም መተሳሰብ መረዳዳትና አብሮነት በእድር ውስጥ ተሳስበው የሚተገበሩ ረቂቅ ሀይሎች ናቸው

የመረዳጃ ዕድሩ የሀይማኖት የዘር የፖለቲካ የዕምነትና የኑሮ ደረጃ ልዩነትን ጥሶ በአባላት ስነልቦና ውስጥ “ለችግርህደራሽ ነኝ” “በጭንቅሽ ጊዜ ከጎንሽ ነኝ” የሚል ጠንካራ የፍቅር መንፈስ የሚያስተላልፍ ተቋም ነው በመንፈስ የሚያስተሳስር ኃይል መራራቅን የሚያከሳ መጨካከንን የሚያመክን ቅን መሰረት ነው

በመሆኑም ይህን መሰረታዊ ሃሳብ ከግንዛቤ ውስጥ በማካተት የመልካም ልሣን ወጣቶች እና ጐልማሶች የመረዳጃ ዕድር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 02 በሀያት 2 የጋራ መኖሪያ በአዲስ እና በአካባቢው ነዋሪዎች በመሰባሰብ እርስ በርስ ለመተጋገዝ ለመረዳዳት እና ለመጠያየቅ ከዚህም ጋር ለልማታዊ እንቅስቃሴ በፍቃደኝነት አቅም የፈቀደውን አስተዋፅኦ ለማድረግ የሚያስችል መመሰረት ተፈላጊ እና አይነተኛ መንገድ ሆኖ ተገኝቷል

በዚህ መሠረት በመሰራች አባላቶች የጋራ ውይይት እና ስምምነት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 በሀያት 02የጋራ መኖሪያ መንደር የመረዳጃ ዕድር የአዲስ አበባ እናየአካባቢውን ነዋሪዎች የሚያቅፍ የመረዳጃ ዕድር በመሆን ተመሥርቷል

ጠቅላላ ድንጋጌ

አንቀጽ 1/አንድ/

የመረዳጃ ዕድሩ ስም

መልካም ልሣን ወጣቶች እና ጐልማሶች የመረዳጃ ዕድር

አንቀጽ 2/ሁለት/

የመረዳጃ ዕድሩ ጽ/ቤትና አርማ

2.1 በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 02 በሀያት 02 የጋራ መኖሪነያ መንደር

2.2 የመረዳጃ ዕድሩ አርማና ማኀተም

አንቀጽ 3 /ሶስት/

የመረዳጃ ዕድሩ አርማ

በዚህ መረዳጃ ዕድር ውሰጥ ተመዝግቦ የሚገኝ ማንኛውም ሰው የዘር የኃይማኖት የነገድና የጐሳ የመሳሰሉትን ልዩነት ሳያደርግ በማንኛውም ረገድ የመንግስትን ሕግ ተከትሎ የዕድርተኛውን አንድነት በማጠናከር ለሞት ለመርዶ እንዲሁም በዕድሩ ደንብ ውስጥ ለተዘረዘሩት ችግሮች መረዳጃ እንዲሆን በበጐ ፈቀደኝነት የተመሰረተ ዕድር ነው

አንቀጽ 4 /አራት/

ትርጓሜ

4.1 ዕድርተኛ ማለት በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ወረዳ 2 በሀየት 02 የጋራ መኖሪያ እና በአዲስ አበባ ነዋሪ መንደር የሆነ ለዕድርተኛነት ተመዝግቦ /ተመዝግባ/ ካርድ የተቀበለ/ች ነዋሪ ሲሆን በልዩ ልዩ ምክንያት ከቀበሌው ክልል ለቆ የሄደ ዕድርተኛ የዕድርተኛነት ግዴታውን የሚፈጽመውን ጭምር ያጠቃልላል

4.2 ጠቅላላ ጉባዔ ማለት ዕድርተኞች በሙሉ በዕድሩ ጉዳይ ላይ ለመወያየትና ውሳኔ ለመስጠት በአንድ በተወሰነ ቦታ ላይ ይህ መተዳደሪያ ደንብ በሚያዘው መሠረት የሚደረግ ስብሰባ ነው

4.3 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማለት በዚህየተሻሻለ ደንብ መሠረት በየሁለት ዓመቱ በጠቅላላ ጉባኤው የሚመረጡ ሊቀመንበር ምክትል ሊቀመንበር ፀሐፊ የሂሳብ ኃላፊ ዋና ገንዘብ ያዥ የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች የንብረት ኃላፊ የቀብርና የመርዶ አስፈጻሚና አዲስ የሚገቡ አባላትን አጣሪ ኮሚቴ ያጠቃለለ ኮሚቴ ነው

44. ባልና ሚስት ማለት በሕግና በባህል ጋብቻ ተጋብተው በአንድ ላይ የሚኖሩና በዕድሩ የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ ተመዝግበው የሚገኙ አብረው የሚኖሩ ማለት ነው

4.5 አባት እናት ማለት የዕድርተኛው/ዋ ወላጅ አባትና እናት በዕድሩ የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ ተሞልተው የሚገኙ ማለት ነው

4.6 ልጅ ማለት የዕድርተኛው/ዋ አብራክ የተገኙና ከጋብቻ ውጭም የተገኙ በዕድሩ የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ ተሞልተው የሚገኙ ማለት ነው

4.7 ዘመድ /ሠራተኛ/ ሲባል ከዕድርተኛው/ዋ ጋር አብሮ በአንድ ቤት የሚኖር ማለት ሲሆን የዕድርተኛው/ዋን ቤት ተከራይቶ አብሮ የሚኖረውን አያካትትም

4.8 የዕለት ቀብር ማለት በዕድርተኛ መኖሪያ ቤት ሰው መቶ አስከሬኑ ከዕድሩ አባል መኖሪያ ቤት ወጥቶ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሲፈፀም ማለት ነው

አንቀጽ 5/አምስት/

የዕድሩ መብትና ግዴታ

5.1 የዕድሩ መብት አንድ የአዲስ አበባ ወይም የሀያት 02 የጋራ መኖሪያ ነዋሪ የሆነ ሰው የዕድሩ አባል ለመሆን ሲጠይቅ በኮሚቴ አጣርቶ የመቀበል መብት አለው

5.1.1 ከእያንዳንዱ አባል የመመዝገቢያ ወርሐዋ መዋጮ የዕቃ ኪራይና የመቀጫ ገንዘብ ይሰበሰባል

5.1.2 በዕድሩ ስም የባንክ ሂሳብ ከፍቶ ገንዘብ ያንቀሳቅሳል

5.1.3 በራሱ ስም ለመክሰስና ለመከሰስ እንዲሁም ማንኛቸውንም ጉዳዮች በግልግል ለመወሰን ይችላል

5.1.4 ማንኛውም ዓይነት ሕጋዊ ውል በራሱ ስም ለመዋዋል ይችላል

አስፈላጊው እንክብካቤ እንዲደረግለት ማንኛውንም ጥረት ያደርጋል

5.1.6 ዕድሩ በስሙ ንብረት የማፍራት ቦታ የመያዝ ጽ/ቤት የመሥራት መብት አለው

5.1.7 ዕድሩ አስፈላጊ የሆኑትን ሠራተኞች የመቅጠር የማስተዳደር የመቅጣትና የማሰናበት መብት አለው

5.2 የዕድሩ ግዴታ

5.2.1 በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 02 በሀያት 02 የጋራ መኖሪያ መንደር የሚኖር ሰው የዕድሩ አባል ለመሆን በጽሑፍ ማመልከቻ ሲያቀርብ ሁኔታው በቀብርና መርዶ አስፈጻሚና አዲስ የሚገቡ አባላት አጣሪ ኮሚቴ አማካይነት ዝርዝር ሁኔታው ተጣርቶ ከቀረበለት በኋላ ለጠቅላላ ጉባዔው በማቅረብ በማስወሰን ኃላፊነት /ግዴታ/ አለበት

5.2.2 ዕድሩ በአባልነት መዝግቦ ለተቀበላቸው ዕድርተኞች የዕለት ቀብርም ሆነ የመርዶ አደጋ ሲያጋጥም በደንብ በአንቀጽ 10/10.ሀ ሐ መ ሠ የተጠቀሰውን ገንዘብ የመክፈል ኃላፊነት አለበት

5.2.3 ዕድሩ በአባልነት ተመዝግቦ ለተቀበለው ዕድርተኛ በእክልም ጊዜ ይሁን በደስታ ዕቃ ሲጠይቅ በደንቡ መሠረት ቆጥሮ የማስረከብ ኃላፊነት አለበት

5.2.4 ዕድሩ እክል በደረሰበት ቤት ዕድርተኞች ተገኝተው ተገቢውን አገልግሎት መስጠታቸውንና የሐዘን ተካፋይ መሆናቸውን የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት

5.2.5 ዕድሩ የወር ተረኞችንና የነጸ አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች እክል በደረሰበት ቤት ተገኝተው ተገቢውን አገልግሎት መስጠታቸውን የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት

አንቀጽ 6 /ስድስት/

የዕድርተኛው መብትና ግዴታ

6. የዕድርተኛው መብት

6.1.1 በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ-02 የሀያት 02አካባቢ የጋራ መኖሪያ ሰፈር ነዋሪዎች መረዳጃ ዕድር አባል ለመሆን የጠየቀ ሰው ምንም ዓይነት ልዩነት ሳያደርግ በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ውሰጥ የተመለከቱትን ዓላማዋችና ተግባሮች መሠረት በማድረግ ዕድሩ የሚጠይቀውን ያሟሉ ሁሉ ዕድርተኛ ለመሆን ይችላል

6.1.2 ዕድርተኛ ለመሆን የሚፈልግ በዕድሩ መተደደሪያ ደንብ አንቀጽ 9.1.1 እና 9.2.1 ውስጥ የተጠቀሰውን የመመዝገቢያ ወርሐዊ መዋጮ መክፈል የሚችል መሆን አለበት

6.1.3 ማንኛውም ዕድርተኛ እክል ሲደርስበት በዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 10.1 ከ”ሀ” ፊደል እስከ “ሠ” ባለው መሠረት የተወሰነውን የገንዘብ እርዳታ በዕለቱ ክፍያው ይፈጸማል ሆኖም ግን ሥራ አስፈጻሚው አጠራጣሪ ነገሮች ከገጠሙት ክፍያውን ከመፈጸሙ በፊት ሁኔታውን ማጣራት አለበት

6.1.4 ማንኛውም ዕድርተኛ እክል ሲያጋጥመው አስፈላጊው እርዳታ እንዲደረግለት በቅርብ ለሚገኘው የዕድር አባል መጠየቅ ይችላል

6.1.5 እክል የደረሰበት ዕድርተኛ ለዕለት ቀብርም ሆነ ለመረዶ የሚያስፈልገውን ዕቃ እንዲቀርብለት ጎድሩን የመጠየቅ መብት አለው

6.1.6 አንድ የዕድር አባል በደስታ ጊዜ ከክልሉ ውጭ ዕቃ በሚጠይቅበት ጊዜ የዕድሩን ዕቃ ተከራይቶ የመውሰድ መብት አለው የማጓጓዣውን ኪራይም የሚከፍለው ተከራዩ ነው

6.1.7 አንድ እድርተኛ ከዚህ ዓለም በመት ቢለይ በሟች መኖሪያ ቤት በጥገኝነት አብሮ የሚኖሩ አባት እናት ልጅ ወንድም እህት በሟች ምትክ በአባልነት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑና ምንም ገቢ የሌላቸው ለመቀጠል ከፈለጉ አንድ የጽሑፍ ማመልከቻ ለዕድሩ በማቅረብ የመመዝገቢያ ገንዘብ ሳይከፍል ወርሐዊ መዋጮ ብቻ በመክፈል በዕድርተኝነት መቀጠል ይችላል

6.1.8 አንድ ዕድርተኛ የዕድር አባል ሆኖ እንዲገባ በጠቅላላ ጉባኤው ከፀደቀለት በኋላ የመመዝገቢያውን ከፍያ ካጠናቀቀ በኋላ በቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ ቤተሰቡን ማስመዝገብ ይኖርበታል

6.1.9 አንድ ዕድርተኛ በዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የመምረጥም ሆነ የመመረጥ ሙሉ መብት አለው

6.1.10 አንድ የዕድር አባል በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት አስፈላጊውን የገንዘብ ዕርዳታና የማቴሪያል እገዛ እንዲሁም እክል ሲደርስበትም ተገቢው አገልግሎት ካልተደረገለት ቅሬታውን ከቻለ በጽሑፍ ካልቻለ በቃል በመጀመሪያ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያቀረበው ቅሬታ ውሳኔ ተሰጥቶት በውሳኔው ቅሬታ ካለው ቅሬታውን ለጠቅላላ ጉባዔ አቅርቦ ያስወስናል ጠቅላላ ጉባኤው የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል

6.1.11 አንድ ዕድርተኛ ክልሉን ከለቀቀ በኋላ የዕድሩ አባል ሆኖ ለመቀጠል ይችላል በዚሁ መሠረት በመተዳደሪያ ደንቡ ውስጥ የተመለከተው መብት እንደተጠበቀ ነው

አንቀጽ 7 /ሰባት/

የዕድርተኛው ግዴታ

7.1 ማንኛውም ዕድርተኛ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ በዚህ ደንብ ውስጥ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች ተግባሮች ግዴታዎችና ኃላፊነቶች ሁሉ አምኖ መቀበሉንና በተግባር ለመተርጐም ግዴታ የገባ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት

7.2 በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ላይ የተመለከቱትን ዕርዳታዎችና አገልግሎቶች ለማግኘት እንዲቻል ዕድርተኛው /ዕድርተኛዋ/ በአንቀጽ 6.1.8 መሠረት ሕጋዊ ባለቤቱን /ባለቤቷንና ልጆቹን /ልጆቿን/ አባቱ /አባቷን/ እናቱ /እናቷን/ በዕድሩ የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ አስቀድሞ ማስመዝገብ ግዴታው ነው የቤተሰብ ቁጥር ሲጨምርበት በየጊዜው ማሳወቅ አለበት

7.3 ማንኛውም ዕድርተኛ የቀብር ወይም የመርዶ ሥነ ሥርዓት የሚፈጸመው ከቀበሌው ውጭ ካልሆነ በስተቀር በሚያደርገው ቅስቀሳ መሠረት በተወሰነው ሰዓት እስከሬን በሚገኝበት ቦታ ወይም በመርዶ ቤት በመገኘት ሥነ ሥርዓቱን የመፈጸም ግዴታ አለበት ከቀብሩም መልስ አስክሬኑ በወጣበት ቤት ተገኝቶ ያስተዛዝናል

7.4 ለዕድሩ ተግባር በማናቸውም ኃላፊነት ተመድቦ እንዲያገለግል ሲመረጥ ተቀብሎ የተመረጠበትን የሥራ ድርሻ በቅንነትና በታማኝት የመፈጸም ግዴታ አለበት

7.5 ማንኛውም ዕድርተኛ የሚደረግለትን ጥሪና ቅስቀሳ መሠረት በጠቅላላ ጉባዔም ሆነ በለሎች የኮሚቴ ስብሰባዎች ምንጊዜም በማናቸውም ስብሰባ ላይ የመገኘት ግዴታ አለበት በዚሁ ስብሰባ ወቅት ወኪል መላክ አይችልም

7.6 የየወሩን ክፍያና ሌላም አስፈላጊ መዋጮዎችን ጠቅላላ ጉባዔው ወይም የሥራ አስፈጻሚው አዲስ የሚገቡ አባላትን አጣሪ ኮሚቴ ወይም ለዳኛና ለፀሀፊ ማሳወቅ አለበት

7.7 ማንኛውም ዕድርተኛ በቤቱ እክል በደረሰበት ጊዜ ለቀብርና ለመርዶ አስፈጻሚና አዲስ የሚገቡ አባላትን አጣሪ ኮሚቴ ወይም ለዳኛና ለፀሐፊ ማሳወቅ አለበት

7.8 ማንኛውም ዕድርተኛ በአንድ የዕድር አባል እክል መድረሱን የሚገልጽ ቅስቀሳ ሲደረግ በአፋጣኝ እክል ወደደረሰበት ቤት በመሄድ አስፈላጊውን እርዳታና አገልግሎተ መስጠት አለበት

7.9 ማንኛውም ዕድርተኛ እክል በደረሰበት ቤት እስከ ሶስት ቀን በመገኘት ሀዘንተኛውን ማጽናናት አለበት

7.10 የዕድሩ ካፒታል ከነበረው ገንዘብ ዝቅ ብሎ ከተገኘ አባላቱ ከወርሃዊ ክፍያ ሌላ በተጨማሪ ጠቅላላ ጉባዔው በሚወስነው መሠረት ድጐማ መክፈል አለበት ክፍያውንም ከወርሃዊ መዋጮ ጋር መክፈል ግዴታው ነው

አንቀጽ 8 /ስምንት/

ስለ አዲስ ገቢ ዕድርተኛ

8.1 የቀበሌው /የአ.አ/ ነዋሪ የሆነ ሰው የዕድሩ አባል ለመሆን ሲፈልግ በዕድሩ አድራሻ ማመልከቻውን ከነቤተሰቡ ዝርዝር ጽፎ ከክላሰር ጋር ለዕድሩ ሰብሳቢ ያቀርባል

8.2 የዕድሩ ሰብሳቢ የቀረበውን ማመልከቻ ለጠቀላላ ጉባዔ በማንበብ ካሰማ በኋላ አመልካች ለጠቅላላ ጉባዔ ያስተዋውቃል

8.3 አጣሪው ኮሚቴ የአመልካቹንና የቤተሰቡን ሁኔታ በዝርዝር በማጥናት በ15 ቀናት ውስጥ ሪፖርት በማድረግ ለዕድሩ ሰብሳቢ ያቀርባል

8.4 ከጠቅላላ ጉባኤ ውስጥ ከሶስት በላይ የአባላት የተቃውሞ ድምጽ ከሰሙና የተቃውሞውም ምክንያት ዕድሩን የሚጐዳ ሆኖ ከተገኘ አመልካቹን ዕድሩ አይቀበለውም

8.5 የዕድሩ ሰብሳቢ የተጠናውን ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤ በማቅረብ ውሳኔ ይሰጣል

8.6 በጠቅላላ ጉባኤው የተሰጠውን ውሳኔ ለአባልነት የሚያበቃው ከሆነ በመተዳደሪያ ደንቡ በአንቀጽ 9.11 ውስጥ የተጠቀሰውን የመመዝገቢያ ክፍያሲጨርስ የአባልነቱን መታወቂያ ደብተር በግዥ ይሰጥዋል

አንቀጽ 9/ዘጠኝ/

የመመዝገቢያና ወርሃዊ ክፍያ አከፋፈል

9.1 የመመዝገቢየ አከፋፈልን በተመለከተ

9.1.1 አንድ አዲስ አባል

9.1.2 የመመዝገቢያውን ክፍያ በአንዴ ለመክፈል የማይችል ከሆነ በቅድሚያ ብር ከከፈለ በኋላ የሚቀረውን ብር በሁለት ተከታታይ ወር ውስጥ ከፍሎ ያጠናቅቃል

9.1.3 በጠቅላላው የመመዝገቢያውን ክፍያ በሶስት ወራት ውስጥ አጠናቆ ካልጨረሰ ያላጠናቀቀበት ምክንያት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ለመሆኑ በጽሑፍ የተደገፈ ማስረጃ በማቅረብ ሁኔታውን በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተጣርቶ ውሳኔ ከተሰጠበት በኋላ የከፈለው ገንዘብ ቢኖር ለዕድሩ ገቢ እንደሆነ ተቆጥሮ ከአባልነት ይሰረዛል

9.1.4 ይኸው አባል የመመዝገቢያውን ክፍያ አጠናቆ ክፍሎ ከመጨረሱ በፊት እከል ቢያጋጥመው በደንቡ ውስጥ የተጠቀሰው የገንዘብ ዕርዳታ አይደረግለትም ነገር ግን ለእንግዳ ማስተናገጃ የዕድሩ ዕቃዎች የሚሰጡት ሲሆን ዕድርተኛውም የሀዘኑ ተካፋይ ይሆናል

9.2 ወርሃዊ ክፍያን በተመለከተ

9.2.1 እያንዳንዱ ዕድርተኛ በየወሩ ብር 200.00 ወርሃዊ መዋጮ የከፍላል ክፍያውንም በተመለከተ በተሰጠው የአባልነት መታወቂያ ደብተር ላይ ተሟልቶ በዕለት ገንዘብ ሰብሳቢው መፈረሙን ያረጋግጣል

9.2.2 ይህንኑ ወርሃዊ ክፍያ በወሩ ውሰጥ ያልከፈለ ቢኖር በተከታዩ ወር የመጀመሪያ ስብሰባ ቀን አጠናቆ መክፈል አለበት

በዚህ መሠረት ሳይከፍል ሲቀር በአንቀጽ 21.2 ከሀ-ሐ በተጠቀሰው መሠረት ቅጣቱን ጨምሮ ይከፍላል

አንቀጽ 10 /አሰር/

ስለ እርዳታ ገንዘብ አከፋፈል

10.1 በዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 9.2.1 መሠረት አሟልቶ በተገኘ በማንኛውም ዕድርኛ ላይ የሞት ወይም የመረዶ /እክል/ በደረሰበት ጊዜ ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘረው የክፍያ ሰንጠረዥ መሠረት ይከፈለዋል

የእክሉ ሁኔታ

አስክሬን ከቤት ሲወጣ

መርዶ

ብር

ብር

እድርተኛው/ዋ ሲሞት

ልጅ ተወልዶ 48 ሰዓት ከኖረ በኋላ ሲሞት

አባት እናት ሲሞት

እህት ወንድም ሲሞት

ዝምድና ኖሮት በጥገኝነት በዕድርተኛው ደጋፊነት በሠራተኝነት በአንድነት ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሲሞት

የመርዶ ክፍያ የማፈጸመው ዘመዱ ለመሞቱ ሟች ከሚኖሩበት አካባቢ ደብዳቤ ጽፎ ሲመጣ ከቅጹ ላይ እንዲሰረዝለት በማድረግና ከሚመለከተው አካል የሞት ሰርተፍኬት ወይም ህጋዊ የኅሁፍ ማስረጃ ተያይዞ ሲቀርብ ነው

የመርዶውም ገንዘብ ወዲያውኑ ከፈለዋል ሆኖም ግን ያለአግባብ ያልመተውን ዘመድ ሞተ ብሎ ክፍያ ቢወስድ የወሰደውን ገንዘብ መልሶ ከዕድሩ ይሰናበታል

ረ. በሠንጠረዡ ውስጥ ከፈደል ሀ-መ የተጠቀሰው ዘመድ ሞቶ አስክሬኑን ወደተፈለገበት ሃገር አጓጉዞ ቢቀበር እሬሳ ከቤት በወጣ ደንብ ይከፈላል

ሰ. በአ/አ ከተማ ክልል እራሱን ችሎ ኑሮ መስርቶ የሚኖር በሰንጠረዡ ውስጥ ከተመለከተው ከፊል ለ-መ የተጠቀሰው ዘመድ ከሞት በኋላም ሆነ ታሞ ወደ ዕድርተኛው ቤት መጥቶ በሞት ለዕድርተኛው ለአባሉ በመርዶ ደንብ ይከፈለዋል ዕድርተኞቹም በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ በመገኘት ይቀብራሉ የዕድር ዕቃም ይሰጠዋል

ሸ. በሰንጠረዡ ውስጥ ከፊደል ለ-መ ከተቀሰው ሀረግ ውጭ የማገኝ ዘመድ ከሞተ በኋላ ዕድርተኛው አስከሬኑን ቤቱ ይዞ ቢመጠ ምንም ዓይነት ክፍያ አይደረግለትም ነገር ግን ዕድርተኛው ዘመዱ ታሞ ለመስታመም ማምጣቲን ከ15 ቀን በፊት ለዕድሩ በጽሑፍ ካሳወቀ /ሪፖርት/ ካደረገ እሬሳ ከቤት ቢወጣ ይከፈላል

ቀ. ከላይ በሰንጠረዥ ውስጥ ከፊደል ለ-መ ከተጠቀሰው ውጭ ከክፍለ ሀገር ወይም ከአዲስ አበባ ውጭ በእንግድነት መጥቶ በድንገት ዕድርተኛው ቤት ቢሞት የቀብር ሥነ ሥርዓት በቤቱ የሚፈፀም ከሆነ እሬሳ ከቤት ቢወጣ ይከፈላል አስክሬኑ ወደ ሌላ ከሄደ ግን ምንም ክፍያ አይደረግም

10.2 በዕድሩ ውስጥ ከአንደ በላይ የሆኑ ወንድማማቾች ወይም እህትማማቾች ቢኖሩ የጋራ የሆነ አባትና እናት እህትና ወንድም በአንድ ዕድርተኛ ቤት ውስጥ ሲሞት እስክሬን ከቤት ለወጣበት ቤት በአንቀጽ 10 በንዑስ አንቀጽ 10.1.ሀ.ለ.ሐ.መ የተመለከተው እርዳታ ይከፈላል ለሌሎች እድርተኞች ግን በመርዶ መልክ የተወሰነወ ይከፈላቸዋል

10.3 በንዑስ አንቀጽ 10.2 እንደተጠቀሰው በዕድሩ ውስጥ ከአንድ የበለጡ ወንድማማቾች እህትማማቾች አባት እናትና ልጅ ቢኖሩና ከእነርሱም አንዱ ቢሞት ለሟቹ በአንቀጽ 10/1-ሀ መሠረት ሙሉ እርዳታ ሲደረግለት ለሌሎች በአንቀጽ 10/1-ለ.ሐ.መ. መሠረት በመርዶ መልክ ይከፈላል

10.3.1 ሟች ቤተሰብ የሌለው ቢሆንና እስከሬኑ ዕድርተኛ ከሆነው ከአንደኛው ወንድም እህት አባት ወይም እናት ቤት ቢወጣ የሟች ሙሉ እርዳታ አስክሬኑ ለወጣበት ቤት ሲከፈል በተጨማሪም አስክሬኑ የወጣበት ዕድርተኛ እንደ ሌሎች ዕድርተኞች ዘመዶቹ በመርዶ ስም ይከፈለዋል

10.3.2 ከዕድርተኛው አንዱ የሞተው የታወቀ ዝምድና ካለው ቤት ሳይሆን በጥገኝነት በሚኖርበት ቤት በሞት ሥርዓተ ቀብሩን ማስፈጸሚያ ውጭ ሆኖ ይከፈላል ከቀብሩ ማስፈጸሚያ ተራፊ የሆነው ገንዘብ አስክሬን ለወጣበት ሟችን በጥገኝነት ላስቀመጠው ሰው አስፈርሞ ይሰጣል

10.3.3 ሟች ዕድርተኛ የሚኖርበት ቤት በጥገኝነት ሳይሆን ራሱን ችሎ ቤት ተከራይቶ የሚኖር ሲሞት የቀበር ሥነ ሥርዓት አስፈፃሚ ኮሚቴ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ካስፈፀመ በኋላ የተረፈውን ገንዘብ ወደ ዕድሩ ግማጃ ቤት ከወጪ ሰነዱ ጋር ገቢ ያደርጋል

10.3.4 አንድ ዕድርተኛ በቤተሰብ ቅጽ ካስመዘገባቸው ዘመዶች በአንድ ቀን ከአንድ ሰው በላይ መርዶ ቢነገረው እርዳታ የሚሰጠው በአንድ ስም ብቻ ሲሆን የሚከፈለውም ከፍተኛው ድርሻ ይሆናል የመቱት ዘመዶች ከቤተሰብ ቅጽ ላይ ይሰረዛሉ

አንቀጽ 11 /አስራ አንድ/

የዕድሩ አመራር አካላትና የሥራ ዘርፍ ኃላፊዎች

ዕድሩ ለሁለት ዓመት እንዲያገለግሉ በጠቅላላ ጉባዔ የሚመረጡ አካላትና ኃላፊዎች ይኖሩታል

ይኸውም 1/ ጠቅላላ ጐባኤ

2/ የሠራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

3/ ኦዲተር

4/ የቀብር የመርዶ አስፈጻሚና አዲስ የሚገቡ አባላትን አጣሪ ኮሚቴ

5/ የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች

አንቀጽ 12 /አስራ ሁለት/

የዕድሩ ጠቅላላ ጉባኤ

12.1 ጠቅላላ ጉባኤው የዕድሩ ከፍተኛው የአመሪር አካል ሆኖ ከታች የተዘረዘሩት ተግባሮች ይኖሩታል

12.1.1 የዕድሩ ዓላማ ተግባራዊነት አጠቃላየ መመሪያ ይወጣል ውሳኔም ይሰጣል የሥራ አስፈጻሚ ኦዲተርና የቀብርና የመርዶ አስፈጻሚና አዲስ የሚገቡ አባላትን አጣሪ ኮሚቴ ይመርጣል ይሰይማል

12.1.2 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢንና የኦዲተር ሪፖርት ያዳምጣል መርምሮም ውሳኔ ይሰጣል

12.1.3 የዕድሩን መተዳደሪያ ደንብ ያፀድቃል እንደ አስፈላጊነቱም ያሻሽላል ወይም ይሽራል

12.1.4 ዕድሩ እንደገና በአዲስ መልክ ተሻሽሎ አንዲቋቋም የመወሰን ሥልጣን አለው

12.1.5 ጠቅላላ ጉባኤው በየ15 ቀናት ይሰበሰባል አስፈላጊ ሆነው ለተገኙ ጉዳዮች መመሪያና ውሳኔ ይሰጣል

12.1.6 በማንኛውም ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከጠቅላላው ዕድርተኛ ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልአተ ጉባኤ ይሆናል ሆኖም የተገኙት ዕድርተኞች ቁጥር ምልአተ ጉባኤውን ሊያሟላ ያልቻሉ እንደሆነ ለሁለተኛ ጊዜ ጥሪ ተደርጐ በተገኘው ጠቅላላ ጉባኤ ከላይ ከ12.1 እስከ 12.1.4 የተዘረዘሩትን ይወሰናል

12.1.7 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሳቢ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ ይሆናል

12.1.8 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፀሐፊ የጠቅላላው ጉባኤ ፀሐፊ የሆናል የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ሁሉ በቃለ ጉባኤ ፀሐፊ ይሆናል የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ሁሉ በቃለ ገባኤ በመያዝ የሠራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ኦዲተሩ ይፈርሙበታል

12.1.9 የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ሁሉ በድምጽ ብልጫ የሚያልፋ ሲሆን እያንዳንዱ እድርተኛ አንድ ድምጽ ይኖረዋል የድምፁ ብዛት እኩል በኩል የሆነ እንደሆነ የጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢ የደገፈው ወገን የጉባኤው ውሳኔ ይሆናል

አንቀጽ 13 /አስራ ሶስት/

የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት

13.1 ዕድሩ 11 አባላትን ያቀፈ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይኖረዋል

13.2 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ከአባሎች ውስጥ ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልአተ ጉባኤ ይሆናል

13.3 ኮሚቴው የሚያሳልፋአቸው ውሣኔዎች ሁሉ በድምጽ ብልጫ ይሆናል ድምጽ እኩል በእኩል ከሆነ ሰብሳቢው ያለበት ወገን ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል

13.4የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በተጨማሪ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል

13.4.1 በሥራ አፈጻጸም ምክንያት በአባላት መካከል የሚነሳውን አለመግባባት ተሰብስቦ ይወስናል

13.4.2 የሠራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማንኛውም የዕድሩን ገንዘብና ንብረት ሰነድ ሁሉ ከቀድሞው የሠራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በአስመራጭ ኮሚቴ አማካይነት የመረከብና የሥራ ዘመኑም ሲፈጸም በዚሁ ዓይነት ለተተካው ኮሚቴ አስመርምሮ የማስረከብ ግዴታ ይኖርበታል

13.4.3 የኮሚቴው አባላት በዚህ ደንብ መሠረት ዕድሩን በሚገባ ታማኝነትና ቅንነት የማስተዳደር ዓላማው ግቡን እንዲመታ የማድረግ የጋራና የግል ኃላፊነት ስላለባቸው ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ በመሰብሰብ አስፈላጊውን ክንውን ይፈጽማሉ

13.4.4 ለጐደለው ወይም አላግባብ ለወጣው ገንዘብና ንብረት የኮሚቴው አባላት በነጠላ አና በውል በኃላፊነት ይጠየቃሉ

13.4.5 ዕድሩ በሚከሰስበት ወይም በሚከስበት ጊዜ የሠራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተነጋግሮ አመቺ በሆነ መንገድ ጉዳዩ ፍጻሜ እንዲያገኝ ይደረጋል

13.4.6 አስፈላጊ የሆነ ንብረቶችን ለመግዛ ሲፈልግ የወጪ ግምቱ ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ ያፀድቃል

አንቀጽ 14 /አስራ አራት/

የዕድሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሥራ ዝርዝር

ሊቀመንበር

ምክትል ሊቀመንበር

ፀሐፊ

የሂሳብ ሹም

ዋና ገንዘብ ያዥ

2 የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች

ኦዲተር

3 የቀብርና የመርዶ አስፈጻሚ አዲስ የሚገባ አባላትን አጣሪ

14.1 የሊቀመንበሩ ተግባራትና ኃላፊነት

14.1.1 የጠቅላላ ጉባኤና የሠራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ያገለግላል

14.1.2 ለጠቅላላ ጉባዔና ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በየደረጃው የሚቀርቡትን የሥራ ጉዳይ አቤቱታዎችን ሪፖርቶችንና ጽሑፎችን በጥንቃቄ እየመረመረ ያቀርባል

14.1.3 በዚህ የመተዳደሪያ ደንብ በጠቅላላ ጉባዔና በሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ የተወሰኑትን ጉዳዮች ሁሉ በሥራ ላይ በትክክል አነዲውሉ አስፈላጊውን መመሪያ ለዕድሩ ኃላፊዎች ሁሉ ይሰጣል በአግባቡ መፈጸሙን ይቆጣጠራል

14.1.4 ጠቅላላ ጉባኤው ወይም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የፈቀደውን የገንዘብ ወጪ ለማዘዝ ስልጣን ይኖረዋል

14.1.5 በዕድሩ ስም ማንኛውንም ሕጋዊ ውል ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እያሳወቀ ለመዋዋል የሚያስፈልገውን ጉዳይ የውክልና ሥልጣን ለመስጠት መብት ይኖረዋል

14.1.6 ለዕድሩ የታመነበት ወጪ ሲያጋጥም ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጋር በመመካከር እስከ ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ የሚደርስ የአንድ ጊዜ ወጪ እንዲወጣ ያዝዛል ከዚህ በላይ ከሆነ ግን ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ ያስወስናል

14.1.7 የዕድሩን የባንክ ሂሰብ በጣምራ ከሂሳብ ሹምና ከዋናው ገንዘብ ያዥ ጋር በመፈረም አስፈላውን ገንዘብ እንዲወጣ ያደርጋል

14.1.8 ጉዳት በደረሰበት ዕድርተኛ ቤት ቀድሞ በመገኘት ያስተባብራል ያልተገኙትም የዕድር አባላት ይቆጣጠራል

14.1.9 ለዕድሩ አገልግሎት የሚሰጡትን ሠራተኞች ከሥራ አስፈጻሚ ጋር በመመካከር ይቀጥራል ይቀጣል ያሰናብታል

14.2 የምክትል ሊቀመንበር ተግባርና ኃላፊነት

14.2.1 ሊቀመንበሩ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ለዕድርተኞች የሚሰጠውን እርዳታና አገልግሎት እየተከታተለ ያስተባብራል ይቆጣጠራልም

14.2.2 ለዕድሩ ገቢ ሊሆኑ የሚገባቸውን ገንዘብና ንብረት ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር በመረዳዳት ገቢ ያስደርጋል

14.2.3 የዕድሩ ንብረት ኃለፊ በመሆን የዕድሩን ቋሚና አላቂ ንብረቶችን በእሱ ኃላፊነት እየተቆጣጠረ ገቢና ወጪ ያደርጋል የዕድሩ ንብረት ጠባቂም ያዝዛል ይቆጣጠራል

14.2.4 የዕድሩ ሊቀመንበር ተግባሩን ለማከናወን በማይችልበት ጊዜ በእርሱ እግር ተተክቶ አስፈላጊውን ተግባር ሁሉ የማከናወን ኃላፊነትና ግዴታ አለበት

14.2.5 ፀሐፊው ተግባሩን ለማከናወን የማይተልበት ጊዜ በእርሱ እግር ተተክቶ አስፈላውን ተግባር ሁሉ ያከናውናል

14.2.6 ሊቀመንበር የሚያዘውን ሌሎች የዕድሩ ጉዳዮች ይፈጽማል

14.3 የዕድሩ ፀሐፊ ተግባርና ኃላፊነት

14.3.1 ጠቅላላ ጉባኤና የሠራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚያሳልፋቸውን ውሳኔዎችንና የሚሰጣቸውን መመሪያዎች በአግባቡ እየተመዘገበ በሥራ ላይ እንዲውሉ ጉዳዩ ለሚመለከተው የሥራ አስፈጻሚ ኀላፊዎች በሊቀመንበሩ በኩል እንዲተላለፍ ያደርጋል

14.3.2 እድሩ ከሌሎች ወገኖች ጋር የሚያደርገውን መጻጻፍና ማንኛውንም የጽሕፈት ሥራዎች እያዘጋጀ ለሊቀመንበሩ ወይም ም/ሊቀመንበሩ እንዲፈርሙበት ያቀርባል

14.3.3 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለጠቅላላ ጉባኤ የሚያቀርበውን የሥራ ሪፖርትና ሌሎችንም መግለጫዎች እያዘጋጀ ለሊቀመንበሩ ያቀርባል

14.3.4 ለዕድርተኞች ወይም ለዕድሩ የሠራ ኃላፊዎች የሚቀርበውን የሠራ ጉዳይ ሪፖርት ወይም አቤቱታ እየተቀበለ ለሊቀመንበሩ በማቅረብ ውሳኔ ይሰጣል

14.3.5 ለጠቅላላው ጉባኤ ወይም ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚቀርቡትን ጉዳዮች ሁሉ በአጀንዳ አስፍሮ ለሊቀመንበሩ ያቀርባል

14.3.6 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን ቃለ ጉባኤ-በጥንቃቄ እያዘጋጀ አባላቱን ካሰፈረመ በኋላ በጥንቃቄ ይጠብቃል

14.3.7 በማንኛውም ዕድርተኛ ላይ በደንቡ የተዘረዘሩት እክሎች በደረሱ ጊዜ እንዲሰጥ ማድረግና በኋላም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየውን ግለሰብ ከቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ እንዲሰረዝ ማድረግ

14.3.8 በየ 15 ቀን በሚደረገው ጠቅላላ ስብሰባ የዕለቱ አጀንዳ ከተጠናቀቀ በኋላ የስም ጥሪ ማድረግ በስብሰባው ዕለት የቀሩትን አባላት የስም ዝርዝር ከቀሩበት ቀናት ጋር በማዘጋጀትና የመቀጫውን ሂሳብ በማሳላት ለዕለት ገንዘብ ስብሳቢዎች ማስተላለፍ

14.3.9 እክል በደረሰበት ቤት በመገኘት ያልተገኘውን ዕድርተኛ የወር ተረኛና የጉልበት ሠራተኞችን መቆጣጠር

14.3.10 ሊቀመንበሩ ወይም ምክትል ሊቀመንበሩ ተግባራቸውን ለማከናወን በማይችሉበት ጊዜ በእነርሱ እግር ተተክቶ አስፈላጊውን ሁሉ ይፈጽማል

14.3.11 ሌሎችንም ሊቀመንበሩ ምክትል ሊቀመንበር የሚያዘውን ተግባራት ይፈጽማል

14.4 የሂሳብ ሹሙ ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት

14.4.1 የገቢና የወጪ መዛግብቶች ደረሰኞችንና ለዕድሩ ሂሳብና ንብረት ሥራ አፈጻጸምና አያያዝ ተገቢ የሆኑትን ሰነዶች ሁሉ የቋቁማል የተቋቋሙትንም በጥንቃቄ ይጠብቃል

14.4.2 ሂሳባቸውን በጊዜው ያልከፈሉትን ዕድርተኞች ዝርዝር ከዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች ጋር በመረዳዳት እያወጣ በየወሩ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቅርቦ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት አፈጻጸሙን ይከታተላል

14.4.3 ከባንክ ገንዘብ ከሊቀመንበር ወይም እሱ ከሚወክለው ሰው ጋር በቼክ ላይ ይፈርማል

14.4.4 ማናቸውም ገንዘብ ሊቀመንበሩ ወይም እሱ የወከለው ኃላፊ ሳያዝበት ወጪ እንዳይሆን ይቆጠራል

14.4.5 ማናቸውም የዕድሩ ገንዘብ በየጊዜው በዕድሩ ባንክ ሂሳብ ውስጥ መግባቱን ያረጋግጣል

14.4.6 ማንኛውም በአግባቡ የተፈቀደ ወጪ ሁሉ ሳይዘገይ ለባለጥቅሙ ማስከፈል የእርሱ ተግባርና ኃላፊነት ይሆናል

14.4.7 የዕድሩ ሂሳብ በኦዲተር እንዲመረመር ተገቢውን ሁሉ ያደርጋል

14.4.8 የሥራ ዘመኑ ተፈጽሞ ሌላ ኀላፊ በሚመረጥበት ጊዜ ሂሳቡን በኦዲተር አስመርምሮ ለተተኪው ኃላፊ አስረክቦ የመሄድ ከፍተኛ የሆነ ኃላፊነት ይኖርበታል

14.4.9 በየ15 ቀኑ ከዕድርተኛው በዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች የሚሰበሰበውን ማናቸውንም ክፍያ ከስፍራው በመገኘት የሂሳቡን ትክክለኛነት አረጋግጦ ለዋናው ገንዘብ ያዥ ርክክብ ያስፈጽማል

14.4.10 ሊቀመንበሩ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል

14.5 የዋና ገንዘብ ያዥ ተግባርና ኃላፊነት

14.5.1 ለዕድሩ ገቢ የሚሆነውን ማንኛውንም ገንዘብ በገቢ ደረሰኝ እየተቀበለ በ3 ቀናት ውስጥ በዕድሩ ባንክ ሂሳብ ውስጥ ገቢ ያደርጋል

14.5.2 ገንዘብ ያዥው የተቀበለውን ገንዘብ ለዕለት አደጋ መጠባበቂያ እንዲሆን የተወሰነውን 10,000/አስር ሺህ ብር/ በእጅ አስቀርቶ አደጋ ለደረሰበት አባል በደንቡ መሠረት ሲታዘዝ ከፍያ በዕለቱ ይፈጽማል

14.5.3 ለዕለት አደጋና ለአስፈላጊ ጉዳዮች ገንዘብ ወጪ ሲያደርግ ገንዘብ ወጪ እንዲያደርግ የማዘዝ ስልጣን በተሰጣቸው በአንድ ሲተዘዝ ወጪ በማድረግ ለታዘዘለት ሰው ወይም ደርጅት በደረሰኝ ክፍያ ይፈጽማል

14.5.3 ለዐለት አደጋና ለአስፈላጊ ጉዳዮች ገንዘብ ወጪ ሲያደርግ ገንዘብ ወጪ እንዲያደርግ የማዘዝ ስልጣን በተሰጣቸው በአንድ ሲታዘዝ ወጩ በማድረግ ለታዘዘለት ሰው ወይም ድርጅት በደረሰኝ ክፍያ ይፈጽማል

14.5.4 ከባንክ ገንዘብ ማውጣት በአስፈለገ ጊዜ ለገንዘብ ወጪ ማዘዣ ስልጣን ከተሰጣቸው ኃላፊዎች ትዕዛዝ ሲደርሰው ገንዘቡን ለማውጣት ከተወከሉት ኃላፊዎች ጋር በመሆን ያወጣል ያወጣውን ገንዘብ በደረሰኝ ይረከባል

14.5.5 ገቢ የተሰበሰበባቸውንና ክፍያ የተፈፀመባቸውን ሰነዶች እንዲሁም ባንክ ገቢው የተደረገበትን የባንክ ደብተር በየጊዜው ለሂሳብ ሹም ያሳያል

14.5.6 በ15 ቀኑ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በመገኘት ከዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎችና ከሌሎች ግለሰቦች በደረሰኝ ገንዘብ ይረከባል

14.5.7 የዕድሩን ገቢና ወጪ የተደረገባቸውን ሰነዶች ለኦዲተር በማቅረብ ያስመረምራል

14.5.8 የገንዘብ ገቢና ወጭ መዝገቦ መዝገብ /ካሽ ቡክ/ ላይ ማናቸውንም ገቢና ወጭ የተደረገባቸውን ሰነደች ይመዘግባል ደረሰኞችን ሳይደልዝና ሳይሰርዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ በመሥራት የተሠራባቸውንና ያለቁትን ጥራዞች እያስመረመረ ለንብረት ኃላፊ ያስረክባል

14.5.9 የሥራ ዘመኑም ሲፈፀም የገንዘብ ምርመራ እንዲደረግ አስፈላጊውን ሁሉ በቅንነትና በታማኝነተ መፈፀምና በመጨረሻም ሕጋዊ ርክክብ የማድረግ ኃላፊነትና ግዴታ ይኖርበታል

14.6 የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች ተግባርና ኃላፊነት

14.6.1 እያንዳንዱ ዕድርተኛ በየወሩ ሊከፍል የሚገባውን ወርሃዊ መዋጮና የመቀጫ ገንዘብ በመቀበል በዋናው መዝገብ ላይ መመዝገብና በዕድርተኛው ካርድ ላይ መዝግቦ ገንዘቡን ለመቀበሉ መፈረም

14.6.2 በዕለቱ የተሰበሰበውን ገንዘብ ወዲያውኑ ለዋና ገንዘብ ያዥ በማስረከብ ያስረከቡበትን ደረሰኝ መረከብ

14.6.3 በየወሩ ወርሃዊ መዋጮ ክፍያውን ያላጠናቀቁትን ከመዝገብ በመልቀም ለሂሳብ ሹም ማቅረብ

14.6.4 ከዕድርተኛው የተሰበሰበውን ገንዘብ ሂሳብ ለመመረመር ለመቆጣጠር በኦዲተርም ሆነ በሂሳብ ሹም በሚጠየቁበት ጊዜ መዝገብና ሰነዶችን አቅርቦ ማስመርመር

14.7 የንብረት ያዢ ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት

14.7.1 ማናቸውንም ቋሚና አላቂ የሆኑ የዕድሩ ንብረቶች ሁሉ በተገቢው መዝገብ መዝግቦ በመያዝ በጥንቃቄ እንዲጠበቁ ያደርጋል

14.7.2 ለዕድርተኞቹ አገልግሎት አንዲውሉ የታዘዙትን ንብረቶች ሁሉ በተዘጋጀው ፎርም ላይ ተፈርሞ እንዲሰጥ ለንብረት ጠባቂ ትዕዛዝ ይሰጣል ሲመለሱም ጉዳት ሳይደርስባቸው መመለሳቸውን ይቆጣጠራል

14.7.3 ሲወገዱ የሚገባቸውን ቋሚ ንብረቶች በጊዜው እንዲጠገኑ የጠፋውን በዓይነት ወይም ዋጋው እንዲተካ እና በተጨማሪም የሚያስፈልገው እንዲሆን ያሳስባል

14.7.4 የዕድሩ ማናቸውንም ንብረት ለመቆጣጠር ኦዲተር በሚጠየቅበት ጊዜ መዝገቦችን ሰነዶችንና ንብረቶችን በስርዓት አዘጋጅቶ ማቅረብ ኃላፊነትና ግዴታ አለበት

14.7.5 የሥራ ዘመኑ ሲፈፀም የንብረት ምርመራ እንዲደረግ አስፈላጊውን ሁሉ በቅንነት እና በታማኝነት መፈፀም እና በመጨረሻ ለተተኪው ርክክብ ማድረግ ይኖርበታል

14.7.6 ሌሎችንም አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎች ሁሉ ከሊቀመንበሩ ወይም ም/ሊቀመንበሩ የሚሰጡትን መመሪያዎች ይፈጽማል

14.8 የቀብርና የመርዶ ሥነ ሥርዓት አስፈጻሚና አዲስ የሚገቡ አባላትን አጣሪ ኮሚቴ የሥራ ተግባር

14.8.1 ተጠሪነቱ ለሊቀመንበሩ ሆኖ አንድ ሰብሳቢ አንድ ፀሐፊና አንድ አባል ይኖሩታል

14.8.2 በዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ የተመለከቱት ሁኔታዎች ሲደርሱ ኮሚቴው ከዕድርተኛው ወይም ከተሰበሰቡ አባላት ጋር በመመካከር በሚየወጡት ኘበሮግራም መሠረት የቀብሩን ወይም የመርዶውን ሥነ ሥርዓት ያከናውናል

14.8.3 ይኸው ከሚቴ የሬሳ ጉድጓድ መቆፈሩንና የሬሳ መኪና በጊዜው የሚቀርብ መሆኑን በማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑትን ግልጋሎቶች ከቤተሰብ ጋር በመመካከር ያስፈጽማል ሆኖም ኮሚቴው አገልግሎቱን ለመስጠት የሚጠይቀው ከዕድርተኛው ወይም ከቤተሰቡ ይቀበላል

14.8.4 ዕድርተኛው ምንም ዓይነት በቤተሰብ መመዝገቢየ ቅጽ ላይ የተመዘገበ ቤተሰብ ከሌለው ይኸው ኮሚቴ የእርዳታውን ገንዘብ ከዕድሩ በመረከብ አስፈላጊው የቀብር ሥነ ሥርዓት ካስፈጸመ በኋላ ምናልባት ተራፊ የሆነ ገንዘብ ካለ በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 10.3.3 /ሀ.ለ/ መሠረት ይፈጸማል

14.8.5 የቀብር ሥነ ሥርዓት በሚፈጸምበት ጊዜ ኮሚቴው በሚያደርገው ቅስቀሳ መሠረት ዕድርተኞች ወደ ሐዘኑ ቤት እንዲሄዱ ማድረግ የቀብር ሥነ ሥርዓት የሚፈጸምበትን ሰዓት ከዕድርተኛው /ከቤተሰብ ጋር ተመካክሮ በመወሰን ዕድርተኛው አስክሬኑን አጅቦ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ወደሚፈጽሙበት ቦታ በመውሰድ ሥነ ሥርዓቱን በትክክል እንዲፈጸም ክትትል ያደርጋል

14.8.6 የዕድሩ አባል ለመሆኑ የሚያመለክተውን ሰው ማመልከትና የቤተሰብ ዝርዝር በመያዝ በአመልካቹ ቤት በመሄድ በጣም የታመመ በሽተኛ መኖሩን የዕድሩን ሕልውና የማይጸረር መሆኑና ግለሰቡ ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ያለውን ማህበራዊ ግንኙነት በዝርዝር በማጥናት ሪፖርት ለሊቀመንበሩ ያቀርባሉ

14.9 የዕድሩ ኦዲተር ተግባርና ኃላፊነት

ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል

14.9.1 የዕድሩ ኦዲተር የዕድሩን ገንዘብና ንብረት አያያዝ አጠቃቀምና አጠባበቅ እንዲሁም ለሥራ አፈጻጸም ያለውን ችግርና ጉድለት ሁሉ ያለምንም ገደብ በመመርመር እንደአስፈላጊነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ዝርዝር ሪፖርት ያቀርባል

14.9.2 የዕድሩ ገንዘብና ንብረት በመመርመር በዓመት አራት ጊዜ በየሶስቱ ወሩ ጠቅላላ ቁጥጥር እያደረገ የተገኘውን ውጤት ለጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት ያቀርባል

14.9.3 በየ 15 ቀን በሚደረገው ስብሰባ ላይ እየተገኘ በዕለቱ የተሰበሰበውን ገንዘብ ለዋና ገ/ያዥ ገቢ መደረጉን ይቆጣጠራል የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎቹንም የአሠራር ስህተት እንዳይፈጠር ዕርዳታ ይሰጣል

14.9.4 በመተዳደሪያ ደንብ ውስጥ የተደረገውንና ጠቅላላ ጉባኤውም የሰጣቸውን መመሪያዎች በሥራ ላይ በሚገባ መዋላቸውን ዝርዝር ምርመራ እያደረገ ስህተት እንዲታረም ተገቢውን ጥረት ሁሉ ያደርጋል

14.9.5 የዕድሩን ገንዘብና ንብረት በሚመረመርበት ጊዜ የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች መዝገብ ከአባላት ካርድ ጋር መመሳከሩን የዋና ገንዘብ ያዥ የተረከበውን ገንዘብ በእጅና በባንክ መኖሩን በየወሩ የገባውንና ያልገባውን ገንዘብ መጠንና በአጠቃላይ የገቢና ወጪ መዝገቦችና ሰነዶች በሚገባ መያዛቸውን ያረጋግጣል

14.9.6 ኦዲተር የሚመለከተው ጥፋትን ብቻ ስላይደለ ችግር ከመድረሱ አስቀድመ ስለንብረትና ገንዘብ አያያዝና አጠባበቅ ተገቢ የሆነ መመሪያ እያዘጋጀ በተግባር ላይ እንዲውል ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊሰጥ ይችላል

14.9.7 ስለ ዕድሩ ገንዘብና ንብረት በራሱ አነነሳሽነት ወይም ከሌላ በሚደርሰው ጥቆማ መሠረት በፈለገበት ጊዜ ምርመራ ማድረግ ይችላል

14.9.8 በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ሁሉ ይሳተፋል ሆኖም ድምጽ አይሰጥም

አንቀጽ 15 /አስራ አምስት/

በየወሩ ስለሚመደቡ የዕድር አባላት የሠራ ድርሻና ኃላፊነት

15.1 የወር ተረኞች ተጠሪነታቸውን ለቀብርና መርዶ ሥነ ሥርዓት አስፈጻሚና አዲስ ለሚገቡ አባላት አጣሪ ኮሚቴ ይሆናል

15.2 እክል በደረሰበት ዕድርተኛ ቤት የሚያገለግሉ 20 የዕድር አባላት በየወሩ ይመደባሉ

15.3 ከተመደቡት ተረኞች መካከል ሁለት አስተባባሪ ተመርጦ በሥራ መሪነትና በተቆጣጣሪነት ይሰየማሉ

15.4 የወር ተረኞች እኩል በደረሰበት ቤት በቅድሚያ በመገኘት ድንኳን በመትከል ወንበር በማዘጋጀትና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑትን ግልጋሎት ይሰጣሉ

15.5 እክል በደረሰበት ቤት በየቀኑ እስከ ሳልስቱ ድረስ በመገኘት እንግዶችን ያስተናብራሉ ሀዘንተኞች ያጽናናሉ ከሴቶች እድር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋሉ

15.6 እኩል በደረሰበት ቤት ያውን የዕድሩን ንብረት በአራተኛው ቀን ከነጻ አገልግሎት ሰጪ ዕድርተኛ ጋር በመሆን ወደ ዕድሩ ግማጃ ቤት በጥንቃቄ ገቢ ያደርጋል

15.7 ያለበቂ ምክንያት በወር ተረኛነት ጊዜ ተገኝቶ አገልግሎት ያልሰጠ አባል በአንቀጽ 21.4 መሠረት ይቀጣል

15.8 የወር ተረኛነት የሥራ አመራር ኮሚቴን አይመለከትም

አንቀጽ 16 /አስራ ስድስት/

ስለ ነጻ አገልግሎት ሰጪዎች

16.1 ዕድሩ በጉልበት ሥራ ብቻ የሚያገለግሉ ከአስር ያልበለጡ የነጻ አገልግሎት ሰጭዎች ይቀበላል

16.2 የነጻ አገልግሎት ሰጭዎች ተጠሪነታቸው ለወር ተረኞች አስተባባሪ ይሆናል

16.3 የነጻ አገልግሎት ሰጭ ለመሆን የሚያመለክት የቀበሌ ሀያት 02 የጋራ መኖሪያ ነዋሪ ሲኖር ጥያቄውንም በጽሑፍ ከክላሰር ጋር ለዕድሩ ሰብሳቢ ያቀርባል

16.4 የዕድሩ ሰብሳቢ በአንቀጽ 8 መሠረት ተፈጻሚ ያደርጋል

16.5 በአንቀጽ 8 መሠረት ሁኔታው ተጠንቶ ለአባልነት የሚያበቃው ሲሆን የመመዝገቢያ የወርሃዊ ክፍያ ሳይጠየቅ የአባልነት መታወቂያ ደብተር ይሰጠዋል

16.6 እንደማንኛውም የዕድር አባል በአንቀጽ 10.1-3 እና 5.2.4 መሠረት የሚደረገው እርዳታ ሁሉ ይሰጠዋል

16.7 በእክል ምክንያተ ሙሉ ዕቃ በተሰጠው ዕድርተኛ ቤት ለሶስት ቀናት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ይጠብቃል ለጠበቀበት ቀናት ብር 1500/አንድ ሺህ አምስት መቶ በየቀኑ ይከፈለዋል ይህም ተፈፃሚ የሚሆነው እክል የደረሰበት ዕድርተኛና የወር ተረኛ አስተባባሪ በትክክል መሥራቱን ሲያረጋግጡለት ብቻ ነው

16.8 አንድ የጉልበት አገልግሎት ሰጪ ዕድርተኛ ነጻ አገለግሎት መስጠት ትቶ ወደ ወር ክፍያ ለመዛወር መጠየቅ የሚችለው ቢያንስ አስር ዓመት በተከታታይ አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ነው ነገር ግን የአገልግሎቱ ጊዜ ሳያልቅ ለመግባት ጥያቄ ካቀረቡ የመመዝገቢያውንና ወርሃዊ መዋጮ ከፍሎ ይገባል

16.9 የነጻ አገልግሎት ሰጪ ዕድርተኛ እከል በደረሰበት ዕድርተኛ ቤት በቅድሚያ በመድረስ ድንኳን ወንበር እና የመሳሰሉትን በማቅረብ ድንኳን ይተክላሉ ወንበር ያዘጋጃሉ በአራተኛው ቀን ድንኳን በማፍረስ ሌሎችንም ዕቃዎች ጭምር ወደ ዕድሩ ግምጃ ቤት በስርዓት ተመላሽ ያደርጋል

16.10 እክል በደረሰበት ቤት እስከ ሶስት ቀን በየዕለቱ በመገኘት አስፈላጊውን አገልግሎት ይሰጣል

16.11 ጠቅላላ ጉባኤው በየ15 ቀኑ በሚሰበሰብበት ዕለት ወንበሮችና አስፈላጊ ዕቃዎችን ማቅረብና መመለስ ይኖርበታል

16.12 ከዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ ከአንዳቸው እክል የደረሰ መሆኑ ሲነገር /በተለይ መርደን በተመለከተ/ ለ20ዎች የወር ተረኞች በየቤታቸው በመሄድ ጥሪ ያደረጋል እንዲሁም ለተገኘው የዕድር አባል ይነግራል

16.13 ለስብሰባ ጊዜና በዕድርተኛ ቤት የሞት አደጋ በደረሰ ጊዜ በተራው ከቅርብ ኃላፊ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጥሩንባ ድምጽ ቅስቀሳ ይደረጋል

16.14 የነጻ አገልግሎት ሰጪ የተሰጠውን ኃላፊነት በሚገባ ካልተወጣ በአንቀጽ 21/1 ከሀ-ሐ 21.3 /ከሀ-ሐ 21/4 መሠረት ይቀጣል

አንቀጽ 17 /አስራ ሰባት/

ስለ ዕድሩ መዛግብትና ሰነዶች

ዕድሩ የሚጠቀምባቸው ልዩ ልዩ መዛግብትና ሰነደች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል

17.1 የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ይህ ደረሰኝ ተከታታይ ቁጥሮች የሚኖሩትን በማተሚያ ቤት የሚታተም ነው ደረሰኞቹ ሶስት የተለያዩ ቅጠሎች ሲኖሩት ዋነኛውም ለከፋይ ሁለተኛው ለሂሳብ ክፍል የመጨረሻው ከጥራዝ ጋር ቀሪ የሚሆን ነው በዚህ ደረሰኝ ዋና ገንዘብ ያዥ ብቻ ገንዘብ የሚቀበልበት ነው

17.2 የገንዘብ መክፈያ ደረሰኝ ይህ ደረሰኝ ተከታታዬ ቁጥሮች የሚኖሩተና በማተሚያ ቤት የሚታተም ነው ደረሰኙ ሁለት የተለያየ ቅጠሎች ሲኖሩት ዋነኛው ለሂሳብ ክፍል ቀሪው ከጥራዙ ጋር ይሆናል

17.3የገቢና የወጩ የሂሳብ መዝገብ ይህ መዝገብ የሚያገለግለው የዕድሩን ማናቸውም የካዝናና የባንክ ገቢና ወጪ ገንዘብ የሂሳብ ኃላፊው የሚመዘግብበት ነው በዚህ መዝገበ ወሱጥ ቀን የገቢው ወይም የወጪው ገንዘብ ምክንያት የደረሰኝ ቁጥር የሚመዘገብበት ኰለም የገቢ ኰለም የወጪ ኰለም የሚዛን ኰለም ይኖሩታል ምዝገባው በየወሩ ከ1 እስከ 30 እየተከናወነ በወሩ መጨረሻ መዘጋት ይኖርበታል

17.4 የዕለት ገንዘብ መቀበያ መዝገብ ይህ መዝገብ በዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች እጅ የሚቀመጥ ሲሆን በየ15 ቀኑ ካአባላት ወርሃዊ መዋጮ መቀጫና መመዝገቡን ተቀብለው በየአባላቱ ስም አኳያ የሚመዘገቡት ነው

17.5 የቋሚ ንብረት መመዝገቢያ መዝገብ ማናቸውም ዕድሩ በቋሚነት ያለው ንብረትና ወደፊትም የሚገዛው ንብረት የሚመዘገብበት ነው መዝገቡም ተራ ቁጥር ዕቃው የተገዛበት ቀን የዕቃው ዓይነት ብዛት ያንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ የሚሰፍሩበት ኰለሞች ይኖሩታል

17.6 የዕድርተኛው ስም ዝርዝር የሚመዘገብበት የባሕር መዝገብ

ዕድሩ ዕድርተኛውን የሚመዘግብበት አንድ ቋሚ የባሕር መዝገብ ይኖረዋል

17.7 የዕድርተኛው የስም ጥሪ መቆጣሪያ መዝገብ

ይህ መዝገብ በፀሐፊው እጅ የሚገኝ ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ በሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ስም በመጥራት የመጡትንና ያልመጡትን አባነላት ለመቆጣጠር የሚያገለግል ነው

17.8 የኘሮቶኮል መዝገብ ይህ መዝገብ ከዕድሩ የሚጻፋትንና ለዕድሩ የሚመጡትን ደብዳበዎች መመዝገቢያ ነው

17.9 የአባላት መታወቂያ ደብተር ይህ ደብተር አዲስ አባል የመመዝገቢያ ክፍሎ ካጠናቀቀ በኋላ በግል የሚሰጠው ሲሆን አገልግሎቱም የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች ወርሐዊ መዋጮም ሆነ ቅጣት አንዲሁም መመዝገቢያና ልዩ መዋጮ በሚቀበሉበት ወቅት ወዲያውኑ በዚሁ ደብተር ላይ የተከፈለውን በመመዝገብ የሚፈርሙበት ነው አባሉም የከፈለውን ገንዘብ የሚቆጣጠርበትና ለመክፈሉም ሥራ አስፈጻሚው የሚቆጣጠርበት የሚያረጋግጥበት ነው

17.10 የጥሬ ገንዘብ ገቢና ወጪ መመዝገቢያ መዝገብ /ካሽ ቡክ/

ይህ መዝገብ ዋና ገንዘብ ያዥ በየጊዜው በደረሰኝ የሚቀበለውና የሚከፍለውን ገንዘብ የሚመዘግብበትና ከወጪ ቀሪውን የሚገልጽ ነው

አንቀጽ 18 /አስራ ስምንት/

ስለ ዕድሩ ንብረት አጠባበቅ

18.1 ማንኛውም የዕድሩ ንብረት የሚቀመጠው በዕድሩ ዕቃ ግምጃ ቤት ውስጥ ይሆናል

18.2 የዕድሩን ጽ/ቤትና ንብረቶች የሚጠብቅ በደመወዝ ተቀጣሪ ሰው ከዕድርተኛው መካከል ይኖረዋል ከዕድርተኛው መካከል የሚቀጠር ከጠፋ ከቀበሌው ነዋሪ ወስጥ ማስታወቂያ በማውጠት አወዳድሮ ይቀጥራል

18.3 የዕድሩን ንብረት ጠባቂ ከዕድሩ ንብረት ኃላፊ የንብረት ኃላፊ ከሌለ ከዕድሩ ሰብሳቢ ወይም ም/ሰብሳቢ በሚደርሰው የጽሑፍ ትዕዛዝ የሚፈለገውን የዕቃ ዓይነቶች ዕቃውን ለሚፈልገው አባል ወይም ተከራይ ለሆነ ሰው በዕቃ ማስረከቢያ ፎርም ላይ በዝርዝር ሞልቶ ያስረክባል በሚያስረክብበት ጊዜም የዕቃው ደህንነት በማሳየት ለሚረከበው አባል ወይም ተከራይ ሰው አስፈርሞ ይሰጣል

18.4 የዕድሩ ዕቃ ተመላሽ በሚሆንበት ጊዜ የንብረት ኃላፊው በንብረቱ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳትና ጉድለት ያልደረሰ መሆኑን በትክክል ተቆጥሮ በሚረጋገጥ መረከብ አለበት ሆኖም ግን ንብረት ክፍሉ ዕቃው ተመላሽ በሚሆንበት ጊዜ ጉዳት የደረሰበትን ዕቃ ተቆጣጥሮ ሳይረከብ ገቢ ቢያደርግ በመጀመሪያ ጉዳት የደረሰባቸውን ንብረቶች ያሠራል የጠፋውንም በራሱ ወጪ ገዝቶ ይተካል በእነዚህ አበላትም በቸልተኝነቱ

ሀ/ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ይቀጣል

ለ/ ለሁለተኛ ጊዜ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ይቀጣል

ሐ/ ለሶስተኛ ጊዜ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/

በዚህም ካልታረመ በጽሑፍ ከዕድሩ ይሰናበታል

18.5 ዕቃዎች ወጪ ሲሆኑም ሆነ ተመላሽ ሲሆኑ ወደያውኑ ለንብረት ኃላፊው ሪፖርት ማቅረብ አለበት

አንቀጽ 19/አስራ ዘጠኝ/

ስለ ዕድሩ ዕቃ አሰጣጥ

19.1 ማንኛውም የዕድሩ አባል አደጋ በደረሰበት ጊዜ ከቤተሰቡ ወይም ከዕድርተኛው አንዱን በመወከል ከሚመለከተው ኃላፊ በጽሑፍ በማሳዘዝ የሚፈለገውን ዕቃ በንብረት መረከቢያ ቅጽ ላይ የዕቃዎቹን ዓይነት በመዘርዘር ፈርሞ ይረከባል ከክልል ውጭ ከሆነ የትራንስፖርት ኪራይ የዕድርተኛው ይሆናል

19.2 በቤት ውስጥ ብቻ ለሚሆን ማንኛውም ደስታ ነክ ጉዳዮች ዐድርተኛው ዕቃውን ለመውሰድ ሲያስፈልገውና ዕድርተኛው ከቤተ ውጭ ለመከራየት ከፈለገ እንደማንኛውም ተከራይ ከፍሎ መውሰድ ይችላል

የዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ

19.3

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

የዕቃው ብዛት

ለአባል ተከራ

ለአንድ ቀን

ለሶስት ቀን

ብር

ብር

1

የሸራ ድንኳን 1ኛ ደረጃ

1

2

የሸራ ድንኳን 2ኛ ደረጃ

1

3

ወንበር ባለ ድጋፍ

1

4

አግዳሚ ወንበር

1

5

የብረት ድስት

1

6

ትሪ

1

7

የንፍሮ ማቅረቢያ ሳህን

1

8

ብርጭቆ

1

9

ማንቆርቆሪያ

1

10

ጭልፋ

1

ሀ/ አንድ የዕድር አባል ለደስታም ሆነ ለማንኛውም ዕቃ ተከራይቶ ወስዶ ዕቃው ላይ ጉዳት ቢደርስበት ጉዳት ለደረሰበት ንብረት ከፋይ ነው

19.4 ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሙሉ በውሉ መሠረት በ4ተኛው ቀን መመለስ ካልቻለ የእያንዳንዱ ዕቃ ኪራይ ዋጋ እጥፍ ታስቦበት እንዲከፈል ይደረጋል ተጠያቂም ይሆናል

19.5 ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በአራተኛው ቀን መመለስ ካልቻለ የእያንዳንዱ ዕቃ ማደሻና ማስጠገኛ ዋጋ በአጠፌታ ይከፍላል

19.6 ማንኛውም ዕድርተኛ የሆነ ዕቃው ምንም ጉዳት ያልደረሰበት መሆኑን ከተረጋገጠ ተከራይ ዕቃውን ተመላሽ በሚያደርግበት ጊዜ ዕቃው ምንም ጉዳት ያልደረሰበት መሆኑን አረጋግጦ ማስረከብ አለበት

አንቀጽ 20/ሃያ/

የዕድሩን ንብረት የወሰደ

ለንብረቱ የሚየደርገው እንክብካቤ

20.1 ለአገልግሎት ተብሎ የተወሰደ ዕቃ በንጽህና ተጠብቆ ሳይሰበር ሳይቀደድ ከቁጥር ሳይጐድል በአራተኛው ቀን በዕድሩ ዕቃ ግምጃ ቤት በመመለስ ለንብረት ኃላፊው ያስረክባል ወሳጁ ዕቃውን ምንም ሳይቀደድና ጉድለት ሳይኖር በንጽህና መመለሱ ማረጋገጫ ከንብረቱ ክፍል ይወስዳል

20.2 የተወሰደው ዕቃ ከቁጥር ቢጐድል ወይም ቢሰበር ተመሳሳዩን ዕቃ በወቅቱ በመግዛትና በማሟላት ለዕድሩ ግምጃ ቤት ያስረክባል ሆኖም የጐደለው ዕቃ በአራተኛው ቀን ካልተመለሰ ለእያንዳንዱ ቀን አጠፌታ ይከፍላል

20.3 የተወሰደው ዕቃ ለምሳሌ አንድ ድንኳን ወንበር የመሳሰሉትን ቢቀደድና ቢሰበር ይህንን ለማስጠገኛ ይቻል ዘንድ በዋስትና የተያዘው ብር 45% /አርባ አምስት በመቶ/ ለጥገና ሥራ ዕድሩ ያውለዋል ሆኖም የጥገናው ዋጋ ከተያዘው ገንዘብ በላይ ከሆነ ልዩነቱን ተጨማሪ ገንዘብ ከኪሱ መክፈል ግዴታ ይኖርበታል

አንቀጽ 21 /ሃያ አንድ/

ልዩ ልዩ የቅጣት አፈጻጸምን በተመለከተ

21.1 ጠቅላላ ጉባኤ በሚጠራው ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ያልተገኘ ዕድርተኛ የሚከተለውን ቅጣቶች ይፈፀምበታል

ሀ/ በአንደኛው ስብሰባ ላይ ያልተገኘ ብር 30.00 ይቀጣል

ለ/ በሁለተኛው ስብሰባ ላይ ያልተገኘ ብር 40.00 ይቀጣል

ሐ/ በሶስተኛው ስብሰባ ላይ ያልተገኘ ብር 50.00 ይቀጣል

መ/ በአራተኛው ስብሰባ ላይ ያልተገኘ ብር 60.00 ይቀጣል

ሠ/ በአምስተኛው ስብሰባ ላይ ያልተገኘ ብር 100.50 ይቀጣል

የመጨረሻውም የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል

ረ/ በስድስተኛው ስብሰባ ከዕድሩ ደብዳቤ በጽሑፍ ይደርሰዋል

21.2 ወርሃዊ ከፍያን በየወሩ አጠናቆ ያልከፈለ ዕድርተኛ የሚከተሉት ቅጣቶች ይፈፀሙበታል

ሀ/ አንደኛውን ወር ያልከፈለ ብር 30.00 ይቀጣል

ለ/ በሁለተኛው ወር ያልከፈለ ብር 50.00 ይቀጣል

ሐ/ በሲስተኛ ወር ያልከፈለ ብር 100.00 ይቀጣል

መ/ በአራተኛ ጊዜ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከዕድሩ ይሰናበታል

21.3 በድንኳን ተከላና በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ያልተገኘ ዕቃ ያላጓጓዘ ድንኳን ያልተከለ የዕድሩ አባል ዕድሩ ባዘጋጀው የዕባል መቀጣጠሪያ መዝገብ መሠረትስም ይቆጣጠራል የቀብር ሥነ-ሥርአቱን ካስፈፀመ በኋላ ሀዘንተኛው ቤት ተመልሶ ስም ይቆጣጠራል ወይም ያስሞላል

ሀ/ በወቅቱ ተገኝቶ የመቆጣጠሪያውን ስሙን ያላስሞላና በቀብሩ ሥነ ሥርዓትም

ሆነ በዕቃ ማጓጓዣ በድንኳን መትከል ላይ ያልተገኝ ዕድርተኛ ከዚህ በታች

በተገለጸው መሠረት ቅጣት ይፈጸምበታል

ለ/ ለመጀመሪያ ጊዜ ብር 30.00 ይቀጣል

ሐ/ ለሁለተኛ ጊዜ ብር 50.00 ይቀጣል

መ/ ለሶስተኛ ጊዜ ብር 100.00 ተቀጥቶ የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ

ይሰጠዋል

ሠ/ ከላይ ከፈደል ሀ-መ በተጠቀሰው ቅጣት መሠረት ካልታረመ ከዕድሩ በጽሑፍ

ይሰናበታል

21.4 በወር ተረኝነት ተመድቦ ያላገለገለ አባል ለቀረቡት የእያንዳንዱ ቀን ብር -50.00/ሃምሳ ብር/ ይቀጣል የወር ተረኛ አስተባባሪ በተረኝነት ተመድበው ተገቢውን አገልግሎት ያልሰጡትን ተቆጣጥሮ ያለመሥራቱን በመጨረሻ ወር ላይ ለሥራ አስፈጻሚው ያለመሥራቱን እያወቀ በቸልታ ተረኛውን ለመጥቀም ሪፖርት ባያደርግለትም በተረኛው ቅጣት በእርሱ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል

21.5 የዕድሩ የመተወቂያ ደብተር የጣለ የጠፋበት ያለቀበት የመታወቂያውን ብር -100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍሎ በምትኩ ሌላ ይወስዳል

21.6 ለዕድሩ የሠራ አመራር አባልነት ተመርጦ የሥራ ድርሻውን በሚገባ ያልተወጣ የሚከተሉትን ቅጣቶች ይፈፀምበታል

ሀ/ ለመጀመሪያ ጊዜ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል

ለ/ ለሁለተኛ ጊዜ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ ይቀጣል

ሐ/ ለሶስተኛ ጊዜ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ተቀጥቶ

የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል

መ/ ከሀ-ሐ የተመለከቱት ቅጣቶች ያልተቀበለ የኮሚቴ አባል/ካለ/ የዕድሩ ሰብሳቢ ለጠቅላላ ጉባኤው አቅርቦ ውሳኔ ይሰጥበታል

21.7 አንድ የዕድር አባል ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሚቴ አባልነት እንዲያገለግል አስመራጭ ኮሚቴ በእጩነት አቀርቦ ጠቅላላ ጉባኤው ከመረጠው በኋላ ምርጫውን አልቀበልም ብሎ ምክንያት ቢያቀርብ የቀረበውን ምክንያት ተቀባይነት ካላገኘ እና በማገልግል ፈቃደኛ ካልሆነ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ይቀጣል ፈቃደኛ ያለመሆኑ ተገልጾ ተጽፎ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል የተሰጠውም ደብዳቤ ቀሪ ከግል ማህደሩ ጋር ተያይዞ ይቀመጣል በድጋሚ ዙር ምርጫ ተደርጐ አሁንም ምርጫውን በምክንያት አልቀበልም ካለ ከዕድሩ በጽሑፍ ይሰናበታል

21.8 ከዕድሩ በቀጥታ የሚያሰናብቱ ምክንያቶች

21.8.1 አንድ የዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የዕድሩን መተዳደሪያ ደንብ የሚጸረርና በዕድሩ ስም በዕድሩ ንብረትና ሀብት ያለአግባብ ሕገ ወጥ ድርጊት ቢፈጸም በዕድሩ ገንዘብና ንብረት ቢገለገል በስልጣኑ ተጠቅሞ ገንዘብ ቢያጐድል ደንቡን ባልተከተለ የመንገድ የገንዘብ ክፍያ ቢፈጽም ይኸው ድርጊት በተጨባጭ ማስረጃ ከተረጋገጠበት ከዕድሩ ከመሰናበቱ ሌላ በሕግ እንዲጠየቅ ይደረጋል

21.9 በራስ ፍላጐት በዕድሩ ስለመሰናበት

አንድ የዕድር አባል በራሱ ፍላጐትም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያት ከዕድሩ ሲሰናበት ምንም ዓይነት ክፍያ አይደረግለትም

አንቀጽ 22 /ሃያ ሁለት/

በአስተያየት ስለሚደገፍ ዕድርተኛ

22.1 አንድ ዕድርተኛ በዕድሩ ደንብ መሠረት ተመዝግቦ የተወሰነውን ገንዘብ እየከፈለ ከ5 ዓመት በላይ ከቆየ በኋላ ከሥራ የመውጣት ሰርቶ ለማግኘት የማይችልና ሌላም ዕድርተኛው ሊያውቀው የሚቻል ልዩ ልዩ ችግሮች ሲያጋጥሙትና ወደ ጉልበት አገልግሎት ሰጪነት ለመለወጥ ሲያመለክት መላው ዕድርተኛ አውቆት እንዲዘዋወር ይሆናል

22.2 ዕድርተኛው/ዋ/ ባለቤቱ/ዋ/ በአባልነት መዋጮውን ለ5 ዓመት ሲከፍለ ቆይተው ሠርተው ገቢ ለማግኘት የማይችሉና ከሌላ ዘንደ ምንም ገቡ ለማግኘት የማይችሉ ከሆኑና በገንዘብም ሆነ በጉልበት ለመተባበር የሚያስችላቸው ከሆነ የሚደረግላቸው ዕድርተኛው/ዋ/ በሕይወት እስካሉ ድረስ ለማንኛውም ዕድርተኛ የሚደረገው ዕርዳታ ሁሉ ይደረግላቸዋል ሆኖም ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆቻቸው እነርሱም ተተክተው ነጻ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል

23.2 በዕድር አባልነት ከአንድ ዓመት ያላነሰ የቆየ

23.3 በአዲስ አበባ አካባቢ በወረዳ 02 በሀያት የጋራ መኖሪያ መንደር ነዋሪ የሆነ

አንቀጽ 23 /ሃያ ሶስት/

የአስመራጭ ኮሚቴ ብዛትና ለመመረጥ ብቁ የሚያደርጉ መመዘኛ ነጥቦች

የአስመራጭ ኮሚቴ አምስት አባላት ያሉ በጠቅላላው ጉባኤው በድምጽ ብልጫ የሚመረጡ ይሆናል እነርሱ

24.1 የዕድሩ ዓላማና ተግባርን ጠንቅቆ የማያውቅ

24.2 በዕድር አባልነት ከሶስት ዓመታት በላይ የቆየ

24.3 በሀያት 02 የጋራ መኖሪያ ነዋሪ የሆኑ

አንቀጽ 24 /ሃያ አራት/

የአስመራጭ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት

25.1 ለሥራ አስፈጻሚ አባልነት የሚመረጡትን አጭዎች ከጠቅላላ ጉባኤ በጥቆማ እንዲቀርቡ ያደርጋል

25.2 ለአያንዳንዱ ሥራ አስፈጻሚ አባልነት የሚቀርቡ እጪዎች ለእያንዳንዱ የሥራ ድርሻ 3/ሶስት/ ይሆናል

25.3 የአስመራጭ ኮሚቴው ለሥራ አስፈጻሚነት የሚቀርቡት ዕጩዎች ምርጫ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት የስብሰባውን ሥነ ሥርዓት በሚገባ ይመራል

25.4 ኮሚቴው ከላይ በአንቀጽ 23 የተመለከቱትን መመዘኛዎች ከሚያሟሉት ውስጥ 2 ብቁ የሆኑ ተወዳዳሪዎች መርጦ ለጠቅላላ ጉባኤው ምርጫ እንዲሰጥበት ያቀርባል

25.5 የአስመራጭ ኮሚቴው ከቀድመ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አዲሶች የሥራ



Contact this candidate